image
tmceth ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ የወላይታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአረካ ከተማ ለሚገነባው የቅዱስ ሚካኤል ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን የመሠረት ድንጋይ አስቀመጡ !

ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ የወላይታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአረካ ከተማ ለሚገነባው የቅዱስ ሚካኤል ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን የመሠረት ድንጋይ አስቀመጡ !
ሰኔ 12 ቀን 2017 ዓ.ም [ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ]
ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ የወላይታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በወላይታ ሀገረ ስብከት በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ቤተ ክህነት አረካ ከተማ ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አዲስ ለሚገነባው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ግንባታ የመሠረት ድንጋይ በዛሬው ዕለት አስቀምጠዋል።
ብፁዕነታቸው በዛሬው ዕለት የሚከበረውን የቅዱስ ሚካኤል በዓልን ምክንያት በማድረግ ወደ አረካ ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ያደረጉ ሲሆን በበዓሉ የተገኙ በርካታ ምእመናንን ወንጌል አስተምረው አባታዊ ቃለ ምዕዳን እና ቡራኬ ሰጥተዋል።
በመጨረሻም ብፁዕነታቸው አሁን አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው ቤተ ክርስቲያን በማርጀቱ ምክንያት አዲስ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ለመስራት በማቀድ ሰበካ ጉባኤው ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ለግንባታው መሠረት ድንጋይ በማስቀመጥ ሁሉም አካል ትብብርና ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

Image
Image