image
tmceth የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ብፁዕ አቡነ ዮሐንስን የቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ አድርጎ መረጠ !

ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የአሲዩት፣ ሳሂል ሰሊምና ኢልባዳሪ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ዛሬው ዕለት የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ዋና ጸሐፊ ሆነው ተመርጠዋል። 


የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬው ዕለት በአሌክሳንድርያ ሎጎስ ማዕከል ዓመታዊ ምልዓተ ጉባኤውን ያካሄደ ሲሆን የሥራ ዘመናቸውን ያጠናቀቁትን የቀድሞው የሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ሜትሮፖሊታን ብፁዕ አቡነ ዳንኤልን በማሰናበት ነው ተተኪውን ዋና ጸሐፊ የመረጠው። 


ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ እ.ኤ.አ በ1960 የተወለዱ ሲሆን እ.ኤ.አ ሰኔ 6 ቀን 1993 ዓ.ም በኤጲስቆጶስነት ተሹመዋል።


ቅዱስ ሲኖዶሱ በጉባኤው በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን ከዚሁ ጋር በተያያዘ 3 ረዳት የቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፍትን ምርጫ ያደረገ ሲሆን ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፣ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ እና ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የፓሪስና የሰሜን ፈረንሳይ ጳጳስ የሲኖዶሱ ምክትል ጸሐፊዎች ሆነው ተመርጠዋል። 


ግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)