image
tmceth የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ መስከረም 21 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በምንጃር ሸንኮር አረርቲ ደበረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ለሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ግንባታ የተሠራ የእንጨት ርብራብ በመደርመሱ ምክንያት ለደረሰው አስድንጋጭ አደጋ ሀዘኑን ገለጸ።


መስከረም 22 ቀን 2018 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካውያን የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝደንት መስከረም 22 ቀን 2018 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ እና ለሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በላኩት የሀዘን መግለጫ ለአረርቲ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች፣ በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ እና ለተጎዱ ቤተሰቦች ፈጣሪ መጽናናትን እንዲሰጥ ተመኝተዋል።
ጌታ ሆይ ለሞቱት ሰዎች
የዘላለም እረፍት ስጣቸው
የዘላለም ብርሃን አብራላቸው
በሰላም አሳርፋቸው!