ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ የፊታችን ቅዳሜ ጳጕሜን 1 ቀን 2017 ዓ.ም ሐዋርያዊ ጉዟቸውን በማጠናቀቅ ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ የመለሳሉ !
ነሐሴ 29 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
+++
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ከሁለት ወራት የሰሜን አሜሪካ ቆይታ በኋላ ቅዳሜ ጳጕሜን 1 ቀን 2017 ዓ.ም ወደ መንበረ ፓትርያርክ እንደሚመለሱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ አስታውቋል።
የቅዱስነታቸውን በሰላም ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ መንበረ ክብራቸው መምጣታቸውን አስመልክቶ ደማቅ አቀባበል እንደሚደረግላቸው የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው ቅዳሜ ጳጕሜን 1 2017 ዓ.ም ማለዳ ጠዋት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ የሸገር ከተማና የደቡብ ምዕራብ ሸዋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም የበላይ ጠባቂ ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣በክልል ትግራይ ደቡባዊ ዞን ማይጨውና የራያ ስድስቱ ወረዳዎች አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣የማኅበራት ክትትልና ቁጥጥር ማደራጃ መምሪያ የበላይ ኀላፊ እና ብፁዓን ሊቃነጳጳሳት ፣ ሊቃውንት፣ካህናትና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች በታላቅ መንፈሳዊ ሥርዓት ይቀበሏቸዋል ።
የቅዱስነታቸው ቡራኬ አይለየን !
