በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ውሳኔ መሠረት ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ለተመደቡት ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ ወደ ሀገረ ስብከቱ መግባታቸውን አስመልክቶ የእንኳን ደህና መጡ መርሐ ግብር እየተከናወነ ይገኛል። ግንቦት 26 ቀን 2017 ዓ.ም [ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ] በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ ሌሎች በርካታ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ መጋቢ ተአምራት የአዲስ አበባ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሐፊ፣ የመንበረ ፓትርያርክ ከፍተኛ የሥራ ሐላፊዎች፣ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የሀገረ ስብከቱና የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ሥራ ሐላፊዎችና ሠራተኞች፣ የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎችና ጸሐፊዎች ተገኝተዋል።
