image
tmceth ቅዱስ ሲኖዶስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክን ደቡብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አድርጎ መደበ!

ላለፉት ሁለት ዓመታት ከ6 ወራት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን በሊቀ ጳጳስነት የመሩት ብፁዕ አቡነ ሄኖክ በዛሬው ዕለት በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የደቡብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው ተመድበዋል።

ብፁዕነታቸው በ1997 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አንብሮተ ዕድ የምዕራብ ወለጋ ኤጲስ ቆጶስ ሆነው የተሾሙ ሲሆን ላለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት ቤተ ክርስቲያንን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ሲያገለግሉ ቆይተዋል። 


ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ለብፁዕነታቸው መልካም የአገልግሎት ዘመንን እየተመኘ በስደት ለሚገኘው መላው የደቡብ አፍሪካ ኦርቶዶክሳዊ አማኝ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት ይወዳል።