image
tmceth "ሃይማኖቶች ለሰላም፣ለመከባበር እና ለአብሮነት!" በሚል መሪ ቃል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የምክክር ጉባኤ እየተካሄደ እንደሚገኝ ተገለጸ።

"ሃይማኖቶች ለሰላም፣ለመከባበር እና ለአብሮነት!" በሚል መሪ ቃል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የምክክር ጉባኤ እየተካሄደ እንደሚገኝ ተገለጸ።
ሰኔ 5 ቀን 2017 ዓ.ም [ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ]
ሃይማኖቶች ለሰላም፣ለመከባበር እና ለአብሮነት በሚል መሪ ቃል ሦስተኛው የሃይማኖት ተቋማት ሀገር አቀፍ የምክክር ጉባኤ በባሕዳር ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በጉባኤው ላይ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ አቡነ አብርሃም የባሕርዳር እና ሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያ ኀላፊዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በኢትዮጵያ የሚገኙ የሃይማኖት አባቶች በየተቋሞቻቸው የተጣላውን በማስታረቅ፣የሕዝብ እና የሀገር አንድነት በማስጠብቅ፣ፍቅር እና ሰላምን በማጎልበት ረገድ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እያበረከቱ እንደሚገኙ በጉባኤው ላይ ተገልጿል፡፡
እነዚህ በተቋም ደረጃ እየተሠሩ ያሉ ሥራዎች በማሳደግ ሰላምን በሀገር ላይ ከማረጋገጥ አንጻር አሁናዊ የኢትዮጵያን ችግሮችን ለመፍታት በተቋም ደረጃ በመሰባሰብ እየመከሩ ይገኛሉ፡፡
ጉባኤው በተጠቀሱና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎች ያስተላልፋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ይሀንን ጉባኤ የአማራ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመሆን እንዳዘጋጁት ለማወቅ ተችሏል፡፡
ዘገባው፦ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ነው