ዓለም አቀፍ የቤተክርስቲያን ጉባኤያት
በዓለም አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ተቀዳሚና ተቀባይነት ያላቸው የኢትዮጵያኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንም የምትቀበላቸውና ለሥርዓተቤተክርስቲያን ምንጭነት ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው አበይት ጉባኤያት 3 ናቸው፡፡
እነዚህም
1- ጉባዔ ኒቅያ በ325 ዓም
2- ጉባዔ ቁስጥንጥንያ በ381 ዓም እና
3- ጉባዔ ኤፌሶን በ431 ዓም ናቸው፡፡
1) ጉባኤ ኒቅያ (በ325 ዓ.ም)
የኒቂያ ጉባኤ የተጠራው የአርዮስን ክህደት ለመቃወም ነው፡፡ የአርዮስክህደት መነሻ ያደረገው በምሳ. 8፡22 ያለውን ቃል ነው ማለትም‹‹እግዚአብሔር ዓለማትን ሳይፈጥር አስቀድሞ ፈጠረኝ›› የሚለውንበማንሳት ‹‹ወልድ ፍጡር ነው›› እያለ ማስተማር ጀመረ፡፡ በዚህ አካሄዱብዙዎችን ማሳሳት ጀመረ የእስክንድርያ ሊቀጳጳስ አለ እስክንድሮስ ከክህደቱእንዲመለስ ብዙ ጣሩ ነገር ግን እርሱ ሊመለስ አልቻለም እንደውም ከ320 ጀምሮ ክህደቱን ማስፋፋት ጀመረ፡፡ በዚህ ጊዜ ሊቀ ጳጳሳቱ እለ እስክንድርዮስ100 የሚያህሉ ኤጲስ ቆጶሳትን ሰብስቦ ክህደቱን አስረዳቸው፡፡
ጉባኤውም የአርዮስን ክህደት ከመረመሩ በኋላ አወገዙት ጉዳዩ በእስክንድርያብጥብጥና ሁከታን እያስከተለ በመሄዱ ንጉሱ ቆስጠንጢኖስ የስፔንኑንኤጲስ ቆጶስ ሆስያስን ወደ እስክንድርያ ላከው፡፡ ከኤጲስ ቆጶሳት ጋር ሲወያይሰንብቶ ወደ ንጉሱ ተመለሰ፡፡ ጉዳይ በሽምግልና መፍታት እንደማይቻልለንጉሱ አስረዳው፡፡ ከዚህ በሁዋላ ጉባኤው እንዲደረግ ተወስኗል፡፡
ጉባኤው በአርዮስ ክህደት ላይ ተወያይቶ አርዮስና ተከታዮቹ የወልድን የባህርይአምላክነት በመቃወም የጠቀሳቸው ጥቅሶች የተሳሳቱ እንደሆኑ አስረድቷል፡፡በዚህም መሠረት በምሳሌ 8÷22 የተጠቀሰው ጥቅስ ቃለ እግዚአብሔርወልድ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት ከአብ ባህርይ መገኘቱን (መወለዱን) እንጂእንደፍጡራን ሁሉ ያልተፈጠረ መሆኑን አርዮስ እንዲረዳው የጉባኤውአባቶች ብዙ ደክመዋል፡፡ ከቅዱሳት መጽሐፍትም ቃል እየጠቀሱ ቃለእግዚአብሔር ወልድ የባህርይ አምላክ መሆኑን አስረድቷል፡፡ ወልድ የአብየባህርይ ልጅ አንጂ ያልተፈጠረ መሆኑን ለማስረዳት የተጠቀሱትም (ዮሐ1÷1-14 እና 14÷30 ሮሜ 9÷15 ፤ 1ዮሐ 5÷20) እና እነዚህን የመሳሰሉት ናቸው፡፡
አርዮስ ከክህደቱ ሊመለስ ባለመቻሉ 318 ቅዱሳን አበው በመንፈስ ቅዱስ‹‹እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ›› በመሆን አርዮስንአውግዘው የወልድን አምላክነት የሚገልጽ የሃይማኖት አንቀጽ አፀደቁ፡፡ ቤተክርስቲያንም በ318 ሊቃውንት በ325 ዓ.ም በኒቅያ ጉባኤ የተወሰነውን ውሳኔተቀብላ ታስተምራለች፡፡

2) የቁስጥንጥንያ ጉባኤ (381 ዓ.ም)
የቁስጥንጥንያ ጉባኤን የተሰበሰቡት በ381 ዓ.ም ነው፡፡ ጉባኤውንየተሰበሰቡበት ምክንያቶች የመቅዶንዮስን፣ የአቡሊናርዮስንና የአውሳብዮስንክህደቶች በመስማት ነው፡፡
የመቅዶንዮስ ክህደትም የመንፈስ ቅዱስን ከአብና ከወልድ ጋር በባህርይበመልክ አንድ አይደለም፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከአብ ከሰረፀ አብ እና ወልድምመንፈስ ቅዱስን ከላከና መልዕክተኛ ከሆነ ከእርሱ ጋር ትክክል አይደለምከእነርሱ በታች (ህፁፅ) ነው የሚል ነበር፡፡ ይህ ትምህርቱም በምስራቅ አብያተክርስቲያናት መዛመት ስለጀመረ አንድ መቶ ሃምሳ (150) ኤጲስቆጶሳትበቁስጥንጥንያ በ301 ዓ.ም ተሰብስበው ዐቢይ ጉባኤ አደረጉ፡፡ በዚህ ጉባኤከብሉያትና ከሐዲሳት እየጠቀሱ መንፈስ ቅዱስ ከአብ ቢሰርፅም ከአብናከወልድ ጋር በባህርይ በመለኮት አንድ መሆኑን ከእነርሱ ጋር ትክክል መሆኑን(መዝ. 33፡6፤ ኢሳ. 6፡3፤ የሐዋ. 28፡28) በመጥቀስ ትምህርቱን አውግዘዋል፡፡
በኒቂያ 318 ቅዱሳን አበው የወሰኑትንም አንቀጸ ሃይማኖት በማጠናከርየመንፈስ ቅዱስን አምላክነት በሚገባ ገልጸው ‹‹ከአብ የሰረፀ ጌታ ሕይወትሰጭ በሚሆን በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን ከአብ እና ከወልድ ጋርእንሰግድለታለን እርሱም በነቢያት አድሮ የተናገረው ነው›› ብለው በኒቂያየሃይማኖት ውሳኔ ላይ ጨምረው ወሰኑ፡፡
3) የኤፌሶን ጉባኤ (431 ዓ.ም)
- ጉባኤ ኤፌሶን በ431ዓ.ም በኤፌሶን ከተማ በ200 ሊቃውንት የተካሄደ ነው፡፡የስብሰባው መሪ ቄርሎስ ነበር፡፡
- የስብሰባው ዋና ምክንያት የንስጥሮስ ክህደት ነው፡፡
- ንስጥሮስ የተማረው በአንጾክያ ሲሆን ክህደቱም ለክርስቶስ ሁለት ባህሪያትአሉ፡፡ አምላክም ሰው የሆነው በንጽረት ነው፡፡ ንጽረት ማለትም እመቤታችንየወለደችው ሰውን ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ እርሱአም ወላዲተ አምላክ አትባልምየሚል ነው፡፡
- ንስጥሮስን ተከራክሮ የረታውና መልስ ያሳጣው እስክንድርያዊው ሊቀጳጳስቄርሎስ ነው፡፡ ቅዱስ ቄርሎስ "የእግዚአብሔር ልጅ በማርያም አደረ፡፡በመከራም ጊዜ ተለየው" የሚሉ ንስጥሮስንና ወገኖቹን የተጠቀሰውንየማርያም ልጅ ብቻ ከሆነ ጥያቄ በክህደትና በድፍረት የተከፈተ አፋቸውንአስይዞ ይመልሳቸው እንደነበር የቤተክርስቲያን ፀሐፊዎች ዘግበውታል፡፡
ምንጭ፡- የቤተክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ በብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስካልዕ በከፊል የተወሰደ