ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል

image

ዜና መዋዕል

ዜና መዋዕል `

ብፁዕ አቡነ ሄኖክ

የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

የተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል የበላይ ጠባቂ

1.የግል ማኅደር 

✟ የትውልድ ሥፍራ - በቀድሞ አጠራሩ ወለጋ ጠቅላይ ግዛት ጊምቢ ከተማ 

✟ አድራሻ - አዲስ አበባ ከተማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት 

✟ ስልክ ቁጥር 

+251911132481 

ኢሜይል

archbishophenok@gmail.com

info@archbishophenok.org

2.መንፈሳዊ ትምህርት 

✟ በቂልጡ ካራ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የአብነት ትምህርት ቤት መሪጌታ አእምሮ ከሚባሉ መምህር ንባብና ዳዊት ተምረዋል 

✟ በደብረ ሊባኖስ ገዳም ከየኔታ ቀጸላ ከውዳሴ ማርያም ዜማ እስከ ምዕራፍ ተምረዋል 

✟ በሞጣ አካባቢ በመዘዋወር ከየኔታ ኪነጥበብ የቅኔ ትምህርትን ተምረዋል ፤ 

✟  በዚያው በሞጣ ከየኔታ አእመረ ቅዳሴ ተምረዋል 

✟ በመቀጠልም ወደ ርዕሰ አድባራት መርጦለማርያም ገዳም በመሄድ ከየኔታ ሀብቴ ለአምስት አመታት የቅኔ ትምህርታቸውን በመከታተል አጠናቅቀዋል ፤ 

✟ ከየኔታ ይሁን ዝማሬ መዋሥዕት በመማር አጠናቅቀዋል። 

✟ ከየኔታ ኅሩይ አርባዕቱን ወንጌላት ተምረዋል፡፡ 

3.ዘመናዊ ትምህርት 

✟ አሶ ትምህርት ቤት እና አድቬንቲስት ትምህርት ቤቶች እና በጊምቢ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ትምህርታቸውን ተከታትለዋል 

✟ ከ1994 ዓ.ም ጀምሮ በነቀምቴ መስከረም ሁለተሰ ትምህርት ቤት በመግባት የመሰናዶ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል 

✟ ከአዲስ አበባ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በአካውንቲንግ እና ፋይናንስ በዲፕሎማ ተመርቀዋል። 

✟ የባችለር ዲያግሪያቸውን በንግድ አስተዳደር ከቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል። 

✟ ጀርመን ሀገር ከሚገኘው ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት በፕሮጀክት ማኔጅመንት ከፍተኛ ዲፕሎማ አግኝተዋል 

✟  በሀገረ ጀርመን ከሚገኘው አይ ቢ ኤም አይ በፕሮጀክት ማኔጅመንት የማስተርስ ዲግሪ አግኝተዋል። 

✟ ከአውሮፖ ኢንስቲትዩት ኦፍ ሊደርሺፕ ኤንድ ማኔጅመንት በኢንተርናሽናል ሪሌሽን ሰርተፊኬት አግኝተዋል። 

4. ክህነት 

✟ ነሐሴ 22 ቀን 1997 ዓ.ም የምዕራብ ወለጋ ኤጲስ ቆጶስ በመሆን በብፁዕ ወቅዱስ ዶ/ር አቡነ ጳውሎስ አንብሮተ ዕድ ተሹመዋል። 

✟ በ1990 ዓመተ ምህረት ከብፁዕ አቡነ ዘካርያስ የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅስና ማዕረግን ተቀብለዋል። 

✟ በመርጡለማርያም ገዳም ምንኵስናን ከመምህር አባ ኃ/ኢየሱስ በ1985 ዓ.ም ተቀብለዋል። 

✟ በ1975 ዓ.ም ከብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ማዕረገ ዲቁናን ተቀብለዋል፡፡ 

5. አገልግሎት 

✟ በጸሎተ ማኅበር፣ የልማት ሥራ በመሥራትና አቅመ ደካሞችን በመርዳት የመርጦለማርያም ገዳምን አገልግለዋል፡፡ 

✟ ከዚያ በመቀጠል በጎጃም ክፍለ ሀገር በተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር በቅዳሴና በማኅሌት ሲያገለግሉ ቆይተዋል። 

✟ ከ1994 ዓ.ም ጀምሮ በብፁዕ አቡነ ኤልያስ የወለጋ ሀገረ ስብከት መልካም ፈቃድ የነቀምቴ ገነተ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ዋና አስተዳዳሪ በመሆን እስከ 1997 ዓ.ም ድረስ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በቅንነትና በታማኝነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል። 

✟ ከነሐሴ 1997 - 2011 ዓ.ም የምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ 

✟ ከ1998 - 2011 ዓ.ም በተደራቢነት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ 

✟ በ2001 ዓ.ም በምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት ሥር የነበረው የቄለም ወለጋ ሀገረ ስብከት ራሱን ችሎ እንዲቋቋም በማድረግ እስከ 2011 ዓ.ም ድረስ በተደራቢነት የዚሁ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ 

✟ ከ2008 - 2011 ዓ.ም የአውስትራሊያ እና የኒውዝላንድ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ 

✟ ከ2011 - ጥቅምት 2015 ዓ.ም የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ 

✟ ከጥቅምት 2015 - ግንቦት 2017 ድረስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

✟ ከግንቦት 2017 ዓ.ም ጀምሮ የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ።


6. በብፁዕነታቸው የተሰሩ እና እየተሰሩ ያሉ ዐበይት ተግባራት 

✟ ብፁዕነታቸው ጥቅምት 1998 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት የኦሮምኛ ቅዳሴ ትርጉም እንዲዘጋጅና ለምዕመናኑ ተደራሽ እንዲሆን በማድረግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ከማድረግም በላይ በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን በቋንቋቸው እንዲማሩ እና የኦሮምኛ ቅዳሴ ትርጉም ተዘጋጅቶ ለአገልግሎት እንዲበቃ አድርገዋል። 

✟ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሀገረ ስብከት በክልሉ የሚገኙ ብሔረሰቦች በቋንቋቸው እንዲያገለግሉ ከማበረታታትም በላይ በርካቶች መሠረታዊ እና ከፍተኛ የቲዮሎጂ ትምህርት በመማር የአካባቢውን ሕብረተሰብ ማገልገል እንዲችሉ በማድረግ በከፍተኛ ሁኔታ የኖላዊነት ግዴታቸውን ሲወጡ ቆይተዋል። 

✟ የቄለም ወለጋ ምዕመናን መንፈሳዊ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አገልግሎቶች በቅርበት እንዲያገኙ ለማድረግ ሀገረ ስብከት እንዲደራጅ በማድረግ አስተዋፅኦ አድርገዋል። 

✟ በአውስትራሊያና የኒውዝላንድ አህጉረ ስብከት ከአኃት አብያተ ክርስቲያናት ጋር ያለው ግንኙነት እንዲጠናከር በማድረግና በውጭ የተወለዱ ሕጻናት በምግባርና በሃይማኖት እንዲታነፁ ለማድረግ ከፍተኛ ሥራን ሲሰሩ ቆይተዋል። 

✟ በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በመዘዋወር ሀገረ ስብከቱ በአጭር ጊዜ ውጤታማ የሆነ የአመራር እና የመንፈሳዊ አገልግሎት ሂደትን እንዲከተል አስችለዋል። 

✟ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ የመጀመሪያ በሆነ መልኩ "መዝገበ ሕያዋን" የተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ በማበልጸግ በሻሸመኔ እና ዙሪያው ባሉ ከተሞች የካህናት እና የምዕመናን ቆጠራ እንዲከናወን አድርገዋል። 

✟ ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከልን በመመስረት ፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በሚዲያው ዘርፍ ውጤታማ ለመሆን የሚያስችላትን አስተዋጽኦ የሚያደርግ ተቋም እውን አድርገዋል። 

✟ በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት የሰው ኃይል አስተዳደር ሲስተም በሀገረ ስብከቱ እንዲተገበር ማድረጋቸው እና የሀገረ ስብከቱ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ዕቅድ መር እንዲሆን ማስቻላቸው 

✟ የስብከተ ወንጌል አገልግሎትን በማጠናከር ኢአማንያን ወደ እውነተኛው የክርስቶስ በረት እንዲቀላቀሉ ማድረጋቸው። 

✟ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ለባለጉዳዮች የተሻለ መስተንግዶ ለመስጠት ለመጀመሪያ ጊዜ የቀጠሮ መያዣ እያ የጉዳይ መከታተከያ ( Case Management System ) በማበልጸግ የሚታየውን ውስብስብ ችግር ለመፍታት በብፁዕነታቸው አማካይነት ጥረት እየተደረገ ይገኛል። 

✟ በዚሁ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የአድባራት እና ገዳማትን የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ መር ለማድረግ እና ወቅቱን የተከተለ የመሬት አያያዝ እንዲኖር ለማድረግ የመሬት አስተዳደር ሲስተም በባለሙያዎች እንዲዘጋጅ በማድረግ ወደ ትግበራ እንዲገባ አድርገዋል። 

✟ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር ለሚገኙ የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶች ግንባታ ለማድረግ ከከተማ አስተዳደሩ ለሁለት ክፍላተ ከተሞች መስሪያ በከተማው መካከል ላይ ከ3,500 ካሬ ሜትር በላይ መሬት እንዲሰጥ በማድረግ ትልቅ አሻራ ጥለዋል።

7. ፕሮጀክቶች እና ተቋማት 

✟ ከ2013 - እስከ አሁን የተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል መሥራች ፣ የቦርድ ሰብሳቢ እና የበላይ ጠባቂ 

✟ ከ2014 - እስከ አሁን የኢቲ አርት ሚዲያ የበላይ ጠባቂ 

✟ ከጥቅምት 2015 - ግንቦት 2017 ዓ.ም የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰብሳቢ